አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላርስ ራስሙሰን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
ሚኒስትሮቹ የሁለቱን ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።
በአህጉራዊና ቀጣናዊ የሰላምና ደህንነት ጉዳዮች እንዲሁም በሌሎች ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ በትብብር መስራት በሚያስችላቸው ሁኔታዎች ላይም ውይይት ማድረጋቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያና ዴንማርክ በልማት ትብብር፣ የግብርናውን ዘርፍ በማዘመን፣ የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል፣ በሰብአዊ እርዳታና በሌሎች መስኮችም በጋራ እየሰሩ መሆኑ ይታወቃል።