Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሴቶች ቀንን ትንኮሳዎችን ማስቀረት በሚቻልበት አጀንዳ ላይ በመምክር ማክበር እንደሚገባ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2016(ኤፍ ቢ ሲ) የዘንድሮው ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን ሲከበር ፆታን መሰረት አድርገው የሚሰነዘሩ ትንኮሳዎችን ማስቀረትና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ በሚቻልበት አጀንዳ ላይ በመመክር ሊሆን እንደሚገባ የሴት ማህበራት የሥራ ኃላፊዎች ገለጹ፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህፃናት መብት መሪ ስራ አስፈፃሚ ዘቢደር ቦጋለ ÷ የዘንድሮው ዓለም ዓቀፍ የሴቶች ቀን ለ118ኛ ጊዜ በተለያዩ ስነስርዓቶች እንደሚከበር ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያም ለ48ኛ ጊዜ ሴቶች በማህበረሰቡ ውስጥ ያላቸውን አስተዋፅዖ አጉልቶ በሚያሳይ መልኩ እንደሚከበርም ነው ያነሱት፡፡

በኢትዮጵያ አካል ጉዳተኛ ሴቶች ማህበር ፕሬዚዳንት ዲባቤ ባጫ በበኩላቸው ÷ ሴቶች ከተፅዕኖ ተላቀው እራሳቸውን በእውቀትና ክህሎት በማብቃት መብታቸውን ማስከበር፣ ተሳትፏቸውንም ማሳደግና  ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ መንቀሳቀስ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

የሕግ ተጠያቂነት ላይ ያሉ የአሰራር ክፍተቶችን ለመፍታትም በሴቶች ቀን አከባበር እለት ትኩረት ሊሰጣቸው ከሚገቡ አጀንዳዎች መካከል መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ የኢትዮጵያ ሴት የሕግ ባለሙያ ማህበር ምክትል ዳይሬክተር ቤተልሔም ደጉ ናቸው፡፡

በመራዖል ከድር

Exit mobile version