Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሰቆጣ ቃልኪዳን ትግበራ ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሰቆጣ ቃልኪዳን ትግበራ፣ በምግብና ስርዓተ ምግብ ስትራቴጂ ምክር ቤት ማቋቋም ላይ ያተኮተ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

በመድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው፣ የክልሉ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎን ጨምሮ ሌሎች የክልል፣ የዞንና የልዩ ወረዳ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

በውይይቱ ከሥርዓተ ምግብ ጋር በተያያዘ በገጠር እንዲሁም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ በሚኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎችና ቤተሰቦች ዘንድ የመቀንጨር ችግር በከፋ ሁኔታ እንደሚስተዋል መጠቀሱን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version