አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የኢፍጣር መርሐ- ግብር በአዲስ አበባ አካሂዷል፡፡
በመርሐ-ግብሩ ላይም÷ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች፣ የኢትዮጵያ ሐይማኖቶች ጉባኤ ተወካዮች፣ የአዲስ አበባና የክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ተወካዮች እንዲሁም የሐይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ ኢብራሂም ቱፋ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት÷ በረመዷን ወቅት መጠያየቅና መቀራረብ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ምክር ቤቱ ያዘጋጀው የኢፍጣር መርሐ-ግብርም ይህንን ታሳቢ ያደረገ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ሕዝበ ሙስሊሙም የረመዳንን ወር የተቸገሩትን በመርዳት፣ የተጣላን በማስታረቅና ሌሎች መልካም ተግባራትን በማከናወን ማሳለፍ እንደሚገባውም አስገንዝበዋል፡፡

