Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሁርሶ የኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ሞተራይዝድ ሻለቆችን እያስመረቀ ነው

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት የሰላም ማስከበር ማዕከል የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለሰላም ማስከበር ተልዕኮ ያሰለጠናቸውን የሰላም አስከባሪ ሞተራይዝድ ሻለቆች እያሰመረቀ ነው።

ተመራቂዎቹ የተግባርና የንድፈ ሐሳብ ወታደራዊ ስልጠናዎችን የተከታተሉና ለሰላም ማስከበር ተልዕኮ የሚሰማሩ የሰላም አስከባሪ የ18ኛ እና የ19ኛ ሞተራይዝድ ሬጅመንት ሻለቃ አመራሮችና አባላት ናቸው።

ተመራቂዎቹ ለሰላም ማስከበር ግዳጅ የሚሰማሩት ወታደራዊ ስነ- ምግባርን ጠብቀው ታላቅ ጀብድ ለመፈፀም የተዘጋጁ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያ በሶማሊያ፣ ሩዋንዳ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ቡሩንዲ፣ ኮንጎ እና በሌሎችም ሀገራት በሰላም ማስከበር ተግባር ላይ ግዳጆችን በመወጣት ለዘላቂ ሰላም መስፈን ኃላፊነቷን መወጣቷና እየተወጣች መሆኗን በስነ- ስርዓቱ ላይ ተጠቅሷል።

በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ የአመራር አባላት፣ የሀገር ሽማግሌዎችና አባገዳዎች ተገኝተዋል።

Exit mobile version