አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2016(ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከአሜሪካ የሱዳን ልዩ መልዕክተኛ ቶም ፔሪሎ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች እንዲሁም በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መምከራቸው ተገልጿል፡፡
አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ኢትዮጵያ በሱዳን ሰላም እንዲሰፍን ስታደርግ የነበረውን ጥረት ገልጸዋል።
ሁለቱ ተፋላሚ ሃይሎች ችግሮቻቸውን በሰላማዊ መንገድ በንግግር እንዲፈቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተደረጉ በጎ ጥረቶችን ለልዩ መልዕክተኛው አስታውሰዋል።
ቶም ፔሪሎ በበኩላቸው÷በሱዳን ሰላም እንዲመጣ በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የተደረገውን ጥረት አድንቀዋል።
ሁለቱ አካላት በቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

