Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል አባላት የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል አባላት የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ፡፡

የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ቤተክርስቲያን ካውንሲል መካነ ኢየሱስ ፕሬዚዳንትና የካውንሲሉ ሥራ አስፈፃሚ አባል ቄስ ዮናስ ይገዙ (ዶ/ር)÷ የአንድነት ፓርክንና የአድዋ ድል መታሰቢያን መጎብኘታቸውን ገልጸዋል፡፡

ሁለቱም ታሪካዊ ሥራዎች የሀገርን ገፅታ ከማጉላታቸው በላይ ትውልዱ በሀገሩ እንዲኮራና የድርሻውን እንዲወጣ አደራ የሰጠ ነው ማለታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

የዓድዋ ድል መታሰቢያ ትውልዱ የተዛባ ታሪኩን ያቀናበት ብቻ ሳይሆን ምስክርነት የተገለጠበት አሁን ለጀመርነው ሀገራዊ ምክክር ጉልበትና አቅም መፍጠር የሚችል ነውም ብለዋል።

ጎብኚዎቹ የሀገር በጎ ገፅታን ማስቀጠልና ለሀገር አንድነት መቆም ቁልፍ ጉዳይ መሆኑንም ነው ያመላከቱት፡፡

አንድነት ካለን ያለንን በመጠቀም የሌለንን ማምጣት እንችላለን፤ አንድነት ከሌለን ግን የሌለንን ማምጣት ቀርቶ ያለንንም መጠቀም በፍፁም አንችልም ሲሉም ገልጸዋል፡፡

Exit mobile version