አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕገ-ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 249 የቱርክ ሽጉጥ መያዙን የወረታ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
የጽ/ቤቱ ሃላፊ ኢንስፔክተር አየነው ተፈራ እንደገለጹት÷ ከጎንደር ወደ ወረታ ከተማ ሲጓዝ የነበረ አይሱዙ ተሽከርካሪ በሕገ ወጥ መንገድ በድብቅ ጭኖት የነበረው የጦር መሳሪያ ተይዟል።
ተጠርጣሪዎቹ በተሽከርካሪው የመጫኛ ቦታ ላይ በሞደፊክ መልክ ሻግ በመስራት 249 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጦች ደብቀው መገኘታቸውንና በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳዩ እየተጣራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ሃላፊው በሕገ-ወጥ መንገድ ለመበልጸግ የሚንቀሳቀሱ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማሳሰባቸውንም የከተማው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

