አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የስዊዘርላንድ ኤምባሲ አዲስ የሚያስገነባው ሕንፃ መሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ።
የመሰረተ ድንጋዩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀ ስላሴ እና ከስዊዘርላንድ አቻቸው ኢግናዚኦ ካሲስ አስቀምጠዋል።
ሕንፃው የአምባሳደሩን መኖሪያ ጨምሮ የስብሰባ አዳራሾችንና ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ክፍሎችን ያካተተ ስለመሆኑ ተነግሯል፡፡
የሕንጻው ንድፍ ከኢትዮጵያ የሼህ ሆጀሌ ቤተ-መንግስት ቅርጽን ጨምሮ የተለያዩ ጉዳዮችን ታሳቢ አድርጎ የተዘጋጁ መሆኑ ተገልጿል።
በወንድሙ አዱኛ

