Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሕብረተሰቡ የደም ልገሳ ባህሉን እንዲያሳድግ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕብረተሰቡ የደም ልገሳ ባህሉን በማሳደግ ደም ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች እንዲደርስ የኢትዮጵያ ደም እና ኅብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ጥሪ አቀረበ፡፡

የበጎ ፈቃደኞች ደም ለጋሾች ቁጥር መቀነሱን ተከትሎ በቂ ደም እየተሰበሰበ አለመሆኑን የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሀብታሙ ታዬ ተናግረዋል፡፡

ይህን ለማካካስም መጋቢትን የደም ልገሳ ወር በማለት የሚሰበሰበውን የደም መጠን ከፍ ለማድረግ እየሠሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ማኅበረሰቡ ቀዳሚ የሆነውን የሰብዓዊነት አገልግሎት ደም በመለገስ ኃላፊነቱን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።

በ2016 የበጀት ዓመት ከ427 ሺህ በላይ ዩኒት ደም ለመሰብሰብ ታቅዶ በስምንት ወራት 220 ሺህ ዩኒት ደም ብቻ መሰብሰቡንም አስታውቀዋል፡፡

በሰሎሞን ይታየው

Exit mobile version