Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮ ቴሌኮም ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ከ8 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም ከኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማሕበራት ፌደሬሽን ጋር በመተባበር ከ8 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአጋዥ መሳሪያዎች ድጋፍ አድርጓል።
 
ኢትዮ ቴሌኮም ከፌዴሬሽኑ ጋር በመተባበር ከመላው ሀገሪቱ ለተውጣጡ 500 ለሚሆኑ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ነው ድጋፉን ያደረገው።
 
የመርጃ ቁሳቁሶቹም ዊልቸር፣ ክራንች፣ ነጭ በትርና መስማትን የሚያግዙ መሳሪያዎች መሆናቸው ተጠቁሟል።
 
በዛሬው ዕለትም በአዲስ አበባ ለሚገኙ ጉዳተኛ ተማሪዎች 62 ዊልቸር፣ 25 ክራንች፣ 59 ነጭ በትር እና 53 መስማትን የሚያግዙ መሳሪያዎች በአጠቃላይ 199 ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጓል፡፡
 
ቀሪ የመርጃ ቁሳቁሶቹ በቀጣይ ለክልሎችና ለከተማ አስተዳደሮች እንደሚከፋፈሉም በመርሀ ግብሩ ተገልጿል።
 
በታሪኩ ወ/ሰንበት
Exit mobile version