Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢትዮጵያ ሌሴቶን 2 ለ 1 አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በሁለተኛው ዙር የወዳጅነት ጨዋታ ሌሴቶን 2 ለ 1 አሸንፋለች፡፡

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው የአቋም መፈተሻ (የወዳጅነት ጨዋታ) ሌሴቶ በመጀመሪያው አጋማሽ ሌህሎሆኖሎ ፎቶአኔ ባስቆጠራት ብቸኛ ጎል እየመራች ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡

ይሁን እንጂ በሁለተኛው አጋማሽ ቸርነት ጉግሳ እና ከነዓን ማርክነህ ባስቆጠሯቸው ሁለት ጎሎች ኢትዮጵያ ጨዋታውን 2 ለ 1 ማሸነፍ ችላለች፡፡

በመጀመሪያው ዙር የወዳጅነት ጨዋታ ኢትዮጵያ በሌሴቶ 2 ለ1 መሸነፏ ይታወሳል፡፡

Exit mobile version