አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኒው ዝላንድ በምድሯ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው እንደለሌ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃኪንዳ አርደን ይፋ አደረጉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሯ በሀገሪቱ ላይ ተጥለው የነበሩ ገደቦች ሁሉም ሊባል በሚቻልበት ሁኔታ በነገው እለት እንደሚነሱ አስታውቀዋል።
ትምህርት ቤቶች እና የስራ ቦታዎች ደረጃ 1 በሚባል ህግ መሰረት ሊከፈቱ እንደሚችል የተገለፀ ሲሆን ያለምንም ገደብ መሰባሰብ እና የሀገር ውስጥ ጉዞም ማድረግ እንደሚቻል ተገጿል።
አካላዊ ርቀት አሁንም እንደሚበረታታ ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትሯ የኒው ዝላንድ አለም አቀፍ ድንበሮች ግን ዝግ ሆነው እንደሚቀጥሉ ተነግሯል።
ከሌላ ሀገራት ወደ ኒው ዝላንድ የሚያቀኑ ሰዎችም ለሁለት ሳምንታት በልይቶ ማቆያ የመቆየት ግዴታ እንዳለባቸው ተጠቁሟል።
በኒው ዝላንድ በአሁን ወቅት በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው ካለመኖሩ ባሻገር ላለፉት 17 ቀናት በቫይረሱ የተያዘ አዲስ ሰው አለመገኘቱም ነው የተነገረው።
እንዲሁም በሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ህክምና ክትትል የሚያደርግ ሰው እንደማይገኝ እና በማህበረሰቡ ውስጥ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ካቆመ 40 ቀናት እንደሆነውም ዘገባው አመልክቷል።
ምንጭ፡- ሲኤንኤን

