Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በጋምቤላ ክልል ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ዘላቂ ሰላም ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ተጠየቀ፡፡

በክልሉ አጠቃላይ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በጋምቤላ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ የፌዴራል እና የክልል ጸጥታ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

በውይይቱ በክልሉ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የሚያስችል አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ እንደሚጠበቅም የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version