አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል እና የክልሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በአዲስ አበባ እየተከናወኑ ያሉ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱም የተለያዩ ክልሎች ርዕሳነ-መሥተዳድሮች፣ ሚኒስትሮች እንዲሁም የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤም በኮሪደር ልማት ሥራዎቹ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በዚህም የኮሪደር ልማት ሥራን ከመጀመሩ በፊት ሰባት ወር የወሰደ ጥናት መደረጉን ጠቅሰው÷ ለልማት ተነሺዎች ተመጣጣኝ የሆነ የማካካሻ ሥራ መከናወኑን አስገንዝበዋል፡፡
የልማት ሥራዎቹ የከተማዋን ገጽታ የሚቀይሩ ናቸው ማለታቸውን ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች ጠንካራ የተቋማት ቅንጅት የታየባቸው መሆናቸውንም አስረድተዋል፡፡

