Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አሲዳማ አፈርን በኖራ በማከም ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚገባ የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አሲዳማ አፈርን በኖራ እና በሌሎች የተቀናጁ ስራዎች በማከም ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚገባ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ተናገሩ።

አሲዳማ አፈርን በኖራ በማከም ምርታማነትን ማሳደግን ታሳቢ ያደረገ መርሐ ግብር ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት “የአፈር ጤና ለሀገር ህልውና” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ነው።

በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ መድረክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የማዕድን ሚኒስትሩ ኢ/ር ሃብታሙ ተገኝ እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

100 ሺህ ሄክታር አሲዳማ አፈርን በዚህ ዓመት ለማከም እንደሚሰራ በመርሐ ግብሩ የተገለጸ ሲሆን÷ ይህንንም ለማስፈጸም 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ተዘጋጅቷል ተብሏል፡፡

በለይኩን አለም

Exit mobile version