አዲስ አበባ፣ ሰኔ 1 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በኬንያ የኢፌዲሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም በዛሬው ዕለት ከኬንያ ፓርላማ የመንግስት ተጠሪ ከሆኑት አደን ዱዋሌ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ተወያይተል።
አምባሳደር መለስ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ ለአደን ዱዋሌ ገለጻ አድርገዋል ።
ግድቡ የሚገነባው የኢትዮጵያ ሕዝቦች ከድህነት ለማውጣት እና ለዘመናት የነበረውን የመልማትና የመበልጸግ ምኞት ለማረገጋጥ መሆኑን ገልፀዋል።
የግድቡ ግንባታ መጠናቀቅ ከኢትዮጵያ አልፎ የቀጠናው ውህደት መፋጠን ጉልህ ሚና ይኖረዋል ማለታቸውን በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።
የኬንያ ፓርላማ የመንግስት ተጠሪ አደን ዱዋሌ በበኩላቸው ታላቁ የህዳሴ ግድብ በቀጠናው የሚስተዋለውን የኃይል ዕጥረት ከመቅረፍ ባሻገር ቀጠናውን በማስተሳሰር ቀጠናዊ ውህደትን የሚያፋጥን ፕሮጀክት መሆኑን ተናግረዋል።

