Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመዲናዋ በ3 ዓመታት 12 ሺህ ትናንሽ የልጆች መጫወቻዎች እና የስፖርት ማዘውተሪያዎች ለመገንባት እየተሠራ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሦስት ዓመታት 12 ሺህ ትናንሽ የልጆች መጫወቻዎች እና የስፖርት ማዘውተሪያዎችን ለመገንባት እየተሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

ከንቲባዋ በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን የብስራተ ገብርኤል የስፖርት ማዘውተሪያ መርቀዋል።

ማዘውተሪያው በከተማ አሥተዳደሩ እና በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የተሠራ ነው።

ከተማ አሥተዳደሩ ለስፖርት በሰጠው ትኩረት በከተማዋ የስፖርት መሠረተ ልማቶች በስፋት እየተገነቡ መሆኑንም ከንቲባ ገልጸዋል፡፡

በቀጣይ ሦስት ዓመታትም 12 ሺህ ትናንሽ የልጆች መጫወቻዎች እና የስፖርት ማዘውተሪያዎች ገንብቶ ለማጠናቀቅ እየሠራን ብለዋል፡፡

ይህም በሥነ-ምግባር የታነጸ እና በአካል ብቃት የጎለበተ ጤነኛ ትውልድ ለማፍራት ያግዛል ነው ያሉት።

Exit mobile version