Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከቦሌ ካርጎ እስከ አቃቂ ድልድይ በመሰራት ላይ የሚገኘውን የልማት ስራ በማጠናቀቅ ለህዝብ ክፍት እናደርጋለን- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከቦሌ ካርጎ እስከ አቃቂ ድልድይ በመሰራት ላይ የሚገኘውን የአረንጓዴ ልማት ስራ በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ለህዝብ ክፍት እናደርጋለን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ዛሬ ጠዋት ከቦሌ ካርጎ እስከ አቃቂ ድልድይ በመሰራት ላይ የሚገኘውን የአረንጓዴ ልማት ስራ ተዘዋውረን ጎብኝተናል ብለዋል።

ከተማዋን ጽዱ፣ ውብ እና አረንጓዴ ለማድረግ የተጀመረው የኮሪደር ልማት አካል የሆነው የአረንጓዴ ልማት ስራው የሕጻናት መጫዎቻዎችን፣ መናፈሻዎችን እንዲሁም ለአካባቢው ነዋሪ ግልጋሎት የሚሰጡ ስራዎችን እንዳካተተም ጠቅሰዋል፡፡

እንዲሁም ከ200 ሺሕ ካሬ በላይ ሽፋን ያለው እና ከቦሌ ካርጎ እስከ አቃቂ ድልድይ ድረስ 9 ነጥብ 5 ኪ.ሜ እንደሚረዝም በመግለጽ ስራውን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ለህዝብ ክፍት እናደርጋለን ብለዋል፡፡

Exit mobile version