Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት በመዲናዋ እየተሠሩ ያሉ የልማት ኮሪደር ሥራዎችን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር እየተሠሩ የሚገኙ የከተማ እድሳትና የልማት ኮሪደር ሥራዎችን እየጎበኙ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤም ለምክር ቤቱ አባላት ገለጻ እያደረጉ ነው፡፡

በገለጻቸውም÷ የኮሪደር ልማቱ ዓላማ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ ማድረግ ነው ማለታቸውን የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ሥራ አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ሳቢ የማድረግ ዓላማ እንዳለው አስረድተዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅም ነዋሪውን ተጠቃሚ ከማድረግ ባሻገር÷ ከተማዋ የጎብኚ መዳረሻ እንድትሆን የራሱን አስተዋጽኦ ያበረክታል ነው ያሉት፡፡

በተጨማሪም ከዓለም አቀፍ ከተሞች ጋር ተወዳዳሪ እንድትሆን እንደሚያስችላት አመላክተው÷ የኮሪደር ልማት ሥራውን ለማሳካትም ከሕዝባችን ጋር ሆነን በቁርጠኝነት እየሠራን ነው ብለዋል።

Exit mobile version