Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለአረንጓዴ አሻራ ልማት 67 ነጥብ 1 ሚሊየን ችግኝ እየተዘጋጀ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለመጪው ክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 67 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ችግኝ እየተዘጋጀ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና ቢሮ አስታውቋል።

በቢሮው የተፈጥሮ ሃብት ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ ፈቃዱ ደሳለኝ እንዳሉት÷ ለ2016 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ ልማት ቡና እና ፍራፍሬን ጨምሮ ሌሎች ችግኞችን የማዘጋጀት ሥራ እየተከናወነ ነው፡፡

በዚህም በክልሉ ሁሉም ዞኖች ለቀጣዩ አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በአጠቃላይ 67 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ችግኝ የማፍላት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

ከዚህ ውስጥም 57 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ የሚሆኑት ለተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ የሚውሉ ችግኞች መሆናቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የተናገሩት አቶ ፈቃዱ፤ አሁን ላይ 30 ሚሊየን የሚጠጋ ችግኝ ለቆጠራ መድረሱን ጠቁመዋል።

ከችግኝ ዝግጅቱ ጎን ለጎን የመትከያ ቦታ የመለየት ሥራ እየተከናወነ ቢሆንም በሚፈለገው ልክ እንዳልተሰራ ገልጸው፤ በየደረጃው የሚገኙ የሚመለከታቸው አካላት ቀጣይ ቀሪ ሥራዎችን በፍጥነት ማጠናቀቅ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በመላኩ ገድፍ

Exit mobile version