Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በመስኖ ከለማው የስንዴ ሰብል ከ50 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ተሰብስቧል – ግብርና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በመስኖ ከለማው የስንዴ ሰብል 50 ሚሊየን 864 ሺህ 516 ኩንታል ምርት መገኘቱን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በመስኖ ስንዴ ልማት 3 ሚሊየን ሔክታር በማረስ 120 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለማግኘት ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን የገለጸው ሚኒስቴሩ፤ እስከ ዛሬው ዕለትም 2 ሚሊየን 978 ሺህ 122 ሔክታር መሬት በዘር መሸፈኑን ነው ያስታወቀው፡፡

እስካሁንም 1 ሚሊየን 140 ሺህ 928 ሔክታር በባህላዊ እና 359 ሺህ 38 ሔክታር በኮምባይነር በድምሩ በ1 ሚሊየን 499 ሺህ 966 ሔክታር ላይ የነበረ ሰብል መሰብሰቡ ተገልጿል፡፡

ከዚህም 50 ሚሊየን 864 ሺህ 516 ኩንታል ምርት መገኘቱን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

ከላይ የተገለጸው የመስኖ ስንዴ ልማት ሥራ እየተከናወነ የሚገኘውም÷ በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች፣ አፋር፣ ጋምቤላ፣ ሶማሌ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በሌላ በኩል በዘንድሮ የበልግ ወቅት÷ 3 ሚሊየን 123 ሺህ 797 ሔክታር ለማልማት እየተሠራ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስረድቷል፡፡

ከዚህም 81 ሚሊየን 852 ሺህ 93 ኩንታል ምርት ለማግኘት መታቀዱን ነው የገለጸው፡፡

የበልግ ቅድመ ዝግጅት ሥራዎችም እየተከናወኑ መሆኑን የገለጸው የሚኒስቴሩ መረጃ÷ እስካሁን ድረስ 2 ሚሊየን 740 ሺህ 702 ሔክታር ታርሷል ብሏል፡፡

ከታረሰው ውስጥም 828 ሺህ 763 ሔክታሩ በዘር መሸፈኑን ነው ያስታወቀው፡፡

Exit mobile version