Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

48 ሚሊየን ብር የሚያወጡ ኮንሮባንድ የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮንትሮባንድ ሲዘዋወሩ የነበሩ 48 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንስትራክሽን ሰርቬይ (ቅየሳ) መሳሪያዎች ተያዙ፡፡

የኮንስትራክሽን ሰርቬይ መሳሪያዎቹ በሃዋሳ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት መያዛቸውን የጉምሩክ ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

እቃዎቹ መነሻው ቡሌሆራ በሆነ ተሽከርካሪ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ የቡና ሰነድ በፕሎፕ የታሸገ ቡናን ሽፋን በማድረግ ሲንቀሳቀሱ በተደረገ ፍተሻ ነው የተያዙት፡፡

የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተጠቁሟል፡

Exit mobile version