Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በጣና ሐይቅ ላይ አገልግሎት ለመስጠት የተሠራችው ጣናነሽ ፪ ጀልባ ጅቡቲ ወደብ ደረሰች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ለኢትዮ ፌሪስ ጣና የሀገር ውስጥ የውሃ ትራንስፖርት እንዲያገለግሉ የተገዙት ሁለት ዘመናዊ ጀልባዎች ጅቡቲ ወደብ ደርሰዋል።

ጣናነሽ ፪ የተሰኘችው ዘመናዊ የህዝብ ትራንስፖርት ጀልባ እና ሌላኛዋ መለስተኛ ፈጣን ቃኝ ጀልባ በአሶሳ መርከብ ላይ ተጭነው ይደርሳሉ ተብሎ ከተያዘላቸው አንድ ቀን ቀድመው መጋቢት 23 ጅቡቲ ወደብ ደርሰዋል።

ጣናነሽ ዘመናዊ የሰው ማጓጓዣ እና የመዝናኛ ጀልባ ስትሆን 38 ሜትር ርዝመት እንዳላት ተገልጿል፡፡

ጀልባዋ በአንድ ግዜ 188 ሰዎችን የመጫን አቅም ያላት መሆኑን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መረጃ አመላክቷል፡፡

Exit mobile version