Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ስኬት ለማስቀጠል ያለመ ሰልፍ በድሬዳዋ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከለውጡ በኋላ የተገኘውን ድልና ስኬት ለማስቀጠል ያለመ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እየተካሄደ ነው።

“ለሀገራችን ብልፅግና በኅብረት እንቆማለን!” በሚል መሪ ሐሳብ በለገሀር አደባባይ እየተካሄደ በሚገኘው የድጋፍ ሰልፍ÷ የአሥተዳደሩ ነዋሪዎች እና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡

የሰልፉ ተሳታፊዎችም÷ ድላችንን እንጠብቃለን ለቀጣይ ስኬት በጋራ እንሠራለን፣ ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም፣ የወል ትርክት ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ መሰረት ነው፣ ጠንካራ ኢትዮጵያ በኅብረ-ብሔራዊ ወንድማማችነት ላይ ትገነባለች የሚሉና ሌሎች ለውጡን የሚደግፉ የተለያዩ መፈክሮችን እያሰሙ ነው፡፡

Exit mobile version