Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በትራፊክ አደጋ የ5 ሰዎች ሕይወት አለፈ

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 27፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ በትራፊክ አደጋ የአምስት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ፡፡

አደጋው በወረዳው ቢጣ ጨጋ ቀበሌ ዳራ አካባቢ ትናንት ከቀኑ 8፡30 ላይ መከሰቱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

አደጋው የተከሰተውም የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ከባለሦስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) ጋር በመጋጨታቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዚህም በባጃጁ ውስጥ የነበሩት አራት ሰዎች ወዲያውኑ ሕይወታቸው ሲያልፍ÷ እንዲሁም አንዲት ሴት ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባት ለሕክምና ወደ ጅማ በመጓዝ ላይ ሳለች ሕይወቷ ማለፉ ተመላክቷል፡፡

ቦታው አልፎ አልፎ አደጋ የሚከሰትበት መሆኑን በመገንዘብ አሽከርካሪዎች ፍጥነታቸውን በመቀነስና ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ እንዲያሽከረክሩም ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡

Exit mobile version