Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በለውጡ የተገኙ ስኬቶችን ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ በአዲስ አበባ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በለውጡ የተገኙ ስኬቶችን ለማስቀጠል ያለመ የድጋፍ ሰልፍ በዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ ተካሄደ፡፡

የድጋፍ ሰልፉ “ለሀገራችን ብልጽግና በህብረት እንቆማለን” በሚል መሪ ሃሳብ ነው የተካሄደው፡፡

በድጋፍ ሰልፉ በከተማዋ ከሚገኙ ሁሉም ክፍለ ከተሞች የመጡ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡

የሰልፉ ተሳታፊዎች በለውጡ የተገኙ ስኬቶችን የሚያንጸባርቁ የተለያዩ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡

ከመልዕክቶቹ መካከልም መጋቢት 24 የኢትዮጵያ ትንሳዔ ማብሰሠሪያ ታሪካዊ ቀን ናት፣ እኛ ኢትዮጵያውያን ለሀገራችን ሠላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና የበኩላችንን እንወጣለን፣ ሀገራዊ ለውጡ ኢትዮጵያን የታደገና ህልውናችንን ማስቀጠል ያስቻለ ነው፣ አዲስ አበባን ዘመናዊ ለማድረግ የተጀመረውን ሥራ ዳር እናደርሳለን፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአንድነታችንና የጥንካሬችን መገለጫ ነው የሚሉ እና ሌሎች ይገኙበታል፡፡

Exit mobile version