አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ2016/17 የምርት ዘመን ጂቡቲ ወደብ ከደረሰው 11 ሚሊየን 160 ሺህ 474 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ 10 ሚሊየን 270 ሺህ 266 ኩንታል ወደ ሀገር ውስጥ መጓጓዙ ተገለጸ፡፡
500 ሺህ 480 ኩንታል ኤን ፒ ኤስ ቦሮን የጫነች መርከብም በዛሬው ዕለት ጂቡቲ ወደብ ደርሳለች፡፡
ከ18 ቀናት በኋላም 636 ሺህ 600 ኩንታል ተጨማሪ ኤን ፒ ኤስ ቦሮን ማዳበሪያ ወደብ እንደሚደርስ ይጠበቃል ሲል የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን አስታውቋል፡፡

