Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ለለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ የሚያገለግሉ ከባድ ማሽነሪዎች ከጅቡቲ ወደብ ወደ ሀገር ቤት እየተጫኑ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ የሚያገለግሉ ከባድ ማሽነሪዎች ከጅቡቲ ወደብ ወደ ሀገር ቤት እየተጫኑ መሆኑን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ (ኢባትሎ) አስታወቀ።

ማሽነሪዎቹ በሐረር መርከብ ተጭነው ጅቡቲ ወደብ መራገፋቸውን ያስታወሰው ኢባትሎ÷ አሁን ላይም በከባድ የየብስ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ቤት እየተጫኑ ይገኛሉ ብሏል።

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ እየተገነባ የሚገኘው ግዙፍ የሲሚንቶ ፋብሪካ÷ በቀን ከ10 ሺህ ቶን በላይ ሲሚንቶ የማምረት አቅም እንዳለው ተጠቁሟል፡፡

ለሚ ሲሚንቶ በግንባታ ሒደት ላይ ሆኖ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን÷ ግንባታው ተጠናቅቆ ምርት ማምረት ሲጀምር ከ20 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል መፍጠር እንደሚችል የኢባትሎ መረጃ አመልክቷል፡፡

Exit mobile version