Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በዶዶላ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ15 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአስራ አምስት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

በዞኑ ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ዘርፍ ሃላፊ ኮማንደር ከማል አማን÷ የትራፊክ አደጋው በጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት መከሰቱን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

አደጋው ከሴሮፍታ የሚመጣ ቅጥቅጥ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ወደ መንገድ እየገባ ካለው ሲኖትራክ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ መከሰቱን ተናግረዋል፡፡

በአደጋው ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች በዶዶላና በመዳ ወላቡ ሆስፒታሎች ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በቢቀላ ቱፋ

Exit mobile version