Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ኢንጅነር ታከለ ኡማ ከበጎ ፈቃደኞች ጋር በመሆን በምግባችን ከጓሯችን መርሃ ግብር ችግኝ ተከሉ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ከበጎ ፈቃደኞች ጋር በመሆን በምግባችን ከጓሯችን መርሃ ግብር ችግኝ ተክለዋል።

ከተማ አስተዳደሩ ያስጀመረውን የክረምት በጎ ፍቃድ አስመልክቶ ነው ምክትል ከንቲባው ከ50 የአዲስ አበባ ሰፈሮች የተውጣጡ 50 በጎ ፍቃደኞች ጋር በመሆን በመዘጋጃ ቅጥር ግቢ ውስጥ ችግኝ ተከላ ያካሄዱት።

በዛሬው እለት በተካሄደው የችግኝ ተከላ ላይ የተሳተፉት 50 ወጣቶች በየሰፈራቸው ችግኝ የመትከል ስራ የሚያስተባበሩ መሆኑም ታውቋል።

በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይም ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፥ የዘንድሮው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የከተማ ግብርና መርህ ያደረገና በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሊፈጠር የሚችለውን የምግብ እጥረት ከወዲሁ ለመሙላት ምግባችን ከጓሯችን በሚል መርህ የሚካሄድ መሆኑን አስታውቀዋል።

በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩም የምግብነት ይዘት ያላቸው አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ቡና መትከል እንደሚገባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ገልፀዋል።

በፀጋዬ ንጉስ

Exit mobile version