አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ የተመራ የክልልና የፌደራል አመራሮችን ያካተተ ልዑክ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ለመጎብኘት ጎንደር ከተማ ገብቷል፡፡
የልዑካን ቡድኑም የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አይሻ ሙሐመድን (ኢ/ር) ጨምሮ የአማራ ክልል አመራሮች ያካተተ መሆኑን አሚኮ ዘግቧል፡፡
ልዑኩ ጎንደር አጼ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስም በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ወርቁ ኃይለማርያም እና በጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ባዩህ አቡሀይ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡