Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የቱርኩ ባይራም ቬሊ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ለመስራት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የቱርኩ ባይራም ቬሊ ዩኒቨርሲቲ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን በመወከል በቱርክ የኢትዮጵያ አምባሳደር አደም መሃማድ ተፈራርመዋል፡፡

አምባሳደሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳስታወቁት ÷ ስምምነቱ ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች በጥናት እና ምርምር ዘርፍ በጋራ መስራት ያስችላቸዋል፡፡

ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ከማጠናከር ባለፈ ኢትዮጵያ በትምህርቱት ዘርፍ ለምታደርገው እንቅስቃሴ አዲስ መንገድ እንደሚከፍት አስገንዝበዋል፡፡

የቱርክ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት በትምህርት እድገት፣ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በባህል ልውውጥ ላይ መሰረት ያደረገ እንደሆነም አውስተዋል፡፡

Exit mobile version