አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትንና የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ህጋዊ ሰውነት ለመስጠት የቀረቡ ረቂቅ አዋጆች አፀደቀ።
የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት16ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል።
ምክር ቤቱ በስብሰባውም የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በቀረበው ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ላይ የተወያየው ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን ህጋዊ ሰውነት ለመስጠት የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በአንድ ተቃውሞ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።
በመቀጠልም ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ህጋዊ ሰውነት ለመስጠት የቀረበ ረቂቅ አዋጅን ተመልክቷል።
በረቂቅ አዋጀጁ ዙሪያ የህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በቀረበው ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ላይ የተወያየው ምክር ቤቱ፥ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ህጋዊ ሰውነት ለመስጠት የቀረበ ረቂቅ አዋጅን በ2 ተቃውሞ፣ በ2 ድምጸ ተአቅቦ እና በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

