Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ደስታ ሌዳሞ ሕዝቡ “ጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና” ንቅናቄን እንዲቀላቀል ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞ ሕዝቡ “ጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና” ንቅናቄን እንዲቀላቀል ጥሪ አቀረቡ፡፡

አቶ ደስታ ንቅናቄውን በመቀላቀል 10 ሺህ ብር ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን÷ ሕዝቡም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው የሂሳብ ቁጥር 1000623230248 ድጋፍ በማድረግ ንቅናቄውን እንዲቀላቀል ጠይቀዋል፡፡

ንቅናቄው ሰዎች በየመንገድ ዳሩ ከመጸዳዳት ወጥተው ንጽህናውን በጠበቀ ቦታ የመጸዳዳት ባህላቸውን እንዲያሳድጉ፣ ለዚህ ደግሞ ደረጃቸውን የጠበቁ መጸዳጃዎች እንዲሠሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ መሆኑ ይታወቃል።

Exit mobile version