Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ግብረ-ኃይሉ የትንሣዔ በዓል በሰላም እንዲከበር ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕዝበ ክርስቲያኑ የትንሣዔ በዓልን በሰላም እንዲያከብር በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱ ከተማ አሥተዳደሮች ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ወደ ተግባር መግባቱን የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታወቀ፡፡

ሕዝቡም የአካባቢውን ሰላምና ደኅንነት የሚያውኩ አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከት ለፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠት ከጋራ ግብረ-ኃይሉ ጎን እንዲቆም ተጠይቋል፡፡

ግብረ-ኃይሉ ለመላው የክርስትና ሐይማኖት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡

Exit mobile version