አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የደኅንነት (ሲሲቲቪ) ካሜራዎችንና ሌሎች ግብዓቶችን ለጎንደር ከተማ አሥተዳደር ድጋፍ አደረገ።
የአሥተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ባዩህ አቡሃይ ጎንደር ከተማን ወደ ስልጡን ከተማ ለመቀየር ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን ጠቅሰው÷ አሠራሮችን ለማዘመን በሚደረገው ጥረትም የኢንስቲትዩቱ ድጋፍ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
የተጀመረውን የስማርት ሲቲ ግንባታ በማጠናቀቅ ከተማዋን÷ የቱሪዝም፣ የኮንፈረንስ እና የኢንቨስትመንት ማዕከል ለማድረግ በትኩረት ይሠራል ማለታቸውን የአሥተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ኢ/ር) በበኩላቸው÷ ተቋማቸው ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡