Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

230 ኢትዮጵያውያን ከኦማን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦማን ማቆያ ጣቢያዎች ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን መካከል 230 ያህሉ ዛሬ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

እንዲሁም በኦማን የሚገኙ 1 ሺህ 590 ኢትዮጵያውያንን ዛሬና ሐሙስ በሚደረጉ ሥድስት በረራዎች ወደ ሀገራቸው ለመመለስ መታቀዱን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡

ዛሬ ለተመለሱት ወገኖችም አስፈላጊውን እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተሰራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

Exit mobile version