Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከቱርክ አቻቸው ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃካን ፊዳን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም የጋራ በሆኑ የሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ምክክር አድርገዋል፡፡

በሀገራቱ መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትና አጋርነት ይበልጥ በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውንም በቱርክ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

Exit mobile version