አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶስት ዙር በተከናወነ በረራ በሳዑዲ አረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ ዜጎችን በመመለስ ስራ በዛሬው ዕለት 1 ሺህ 194 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
ወደ ሀገር ከተመለሱት ውስጥ 789 ወንዶች፣ 384 ሴቶች እና 21 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 24 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሆኑ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።
ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ እስካሁን ከ18 ሺህ 500 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል።