አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሀዋሳ ከተማ ከ7 ነጥብ 9 ሚሊየን በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የሳኒታይዘር ማምረቻ ተመርቆ ወደ ማመረት ገባ።
በክልሉ መንግሥት እና ህዝብ ድጋፍ የተገነባው ማምረቻ በክልሉ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ መሆኑም ነው የተነገረው።
የደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጌታሁን ጋረደው እንዳሉት ቀርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ያለ ትርፍ የሚታዩ የተለያዩ የሰብዓዊ አገልግሎቶች ሲያበረክት የቆየና አሁንም መቀጠሉን ጠቁመዋል፡፡
የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከክልሉ መንግሥት ጎን በመሆን ላደረገው ሁሉን አቀፍ ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል።
የደቡብ ክልል ቀይ መስቀል ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ዮሀንስ ለታሞ ዛሬ ለምረቃ የበቃውን የሳኒታይዘር ማምረቻ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ በልዩ ልዩ የሰብዓዊ አገልግሎቶች እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ የሚያስመሰግን ነው ብለዋል።
ከ368 ሺህ በላይ አባላት ያሉት ማህበሩ በክልሉ የሚገኙ 22 ሚሊየን ሰዎችን በማገልገል ላይ እንደሚገኝ በስነ ስርዓቱ ላይ ተጠቁሟል።
በሶዶ ለማና መቅደስ አስፋው

