Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከደቡብ ኮሪያ አቻቸው ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከደቡብ ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካንግ ዩንግ ውሃ ጋር ዛሬ በስልክ ተወያዩ።

ሁለቱ ሚኒስትሮቸ የሁለቱን አገራት ግንኙነት ለማጠናከር፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በትብብር ለመከላከል እና የኮሪያ ባለህብቶች በኢትዮጵያ ስለሚኖራቸው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ በተመለከተ ትኩረት አድርገው መክረዋል።

በውይይቱ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የኢትጵያና የደቡብ ኮሪያ ግንኙነት በደም የተሳሰረ እና ታሪካዊ በመሆኑ ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋጋር የሁለቱን አገራት ህዝቦች ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ ኢትዮጵያ በትኩረት ትሰራለች ነው ያሉት።

ደቡብ ኮሪያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመቆጣጠር ያደረገቸውን ጥረት አድንቀው፤ በዚሁ ዙሪያ ለኢትዮጵያ እያደረገች ስላለው የቁሳቁስ ድጋፍም አመስግነዋል።

እንዲሁም ኮሪያውያን ባለሀብቶች በአትዮጵያ በስፋት መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ መንግስት እንዲያበረታታቸውም አቶ ገዱ በውይታቸው አንስተዋል።

ካንግ ዩንግ ውሃ በበኩላቸው ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ለኮሪያ ነጻነት የከፈሉት መስዋዕትነት በኮሪያውያን ልብ ውስጥ ዘላለም ሲታወስ ይኖራል ያሉ ሲሆን የኮቪድ ወረርሽኝ ዓለም አቀፍ ችግር በመሆኑ ኮሪያ በዚህ ዘሪያ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍም አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።

በተመድ ጥላ ስር በደቡብ ሱዳን ለተሰማራው የኮሪያ ሰላም አስከባሪ ሃይል ኢትዮጵያ ስላደረገችው ድጋፍም ምስጋነቸውን አቅርበዋለ።

ኮሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽና ዓለም አቀፍ ትብብር ይበልጥ አጠናክራ እንደምትቀጥልም ካንግ ዩንግ ውሃ ገልጸው፤የኮሪያ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በስፋት መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱም መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ መግለፃቸውን ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version