Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ፍቃዱ ተሰማ የ #ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄን ተቀላቀሉ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ፍቃዱ ተሰማ ለ #ጽዱኢትዮጵያ 10 ሺህ ብር ድጋፍ በማድረግ ንቅናቄውን ተቀላቅለዋል።

ንቅናቄው ሰዎች ንጽህናውን በጠበቀ ቦታ በመጸዳዳት አካባቢን ንጹህ የማድረግ ባህልን እንዲያሳድጉ ደረጃቸውን የጠበቁ መጸዳጃዎች እንዲሠሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ መሆኑ ይታወቃል።

ለ #ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ ዜጎች ተሳትፎ ማድረጋቸውን የቀጠሉ ሲሆን÷ ከትናንት በስቲያ ብቻ በተካሄደ ዲጂታል ቴሌቶን በአንድ ጀምበር ከ154 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡ ይታወሳል፡፡

Exit mobile version