አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) መከላከያ የጀመረውን መጨረስ የሚችል ያሰበውንም የሚያሳካ ተቋም ነው ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትር አብረሃም በላይ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ሚኒስትሩ በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ይዞታ ስር በነበረው ወሎ ሰፈር ለሚገነባው ከነዓን ታውን ሺፕ የሚኒ ሲቲ ግንባታ ፕሮጀክት የመሠረት ድንጋይ አኑረዋል፡፡
በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግርም÷ ለረጅም ዓመታት በመከላከያ ይዞታ ስር የነበሩ መሬቶች መልማት በሚገባቸው ልክ ሳይለሙ ቆይተዋል ብለዋል።
የወሎ ሰፈር ሚኒ ሲቲ ግንባታ ፕሮጀክት በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ማረጋገጣቸውን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ አመላክቷል፡፡
የከንዓን ታውን ሺፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ በረከት ጎይቶም እንዳሉት የሚኒ ሲቲ ግንባታው ባለ 24 ወለል ዘመናዊ የመኖሪያ አፖርታማዎች፣ የንግድ ደረጃቸውን የጠበቁ የገበያ አዳራሾች፣ ለዕይታ ማራኪና ዘመናዊ መንገዶች፣ የቢሮ ሕንጻዎች፣ ለከተማ መለያ የሚሆን የተዋበ የአርክቴክት ውጤትን ያካተተው ፡፡

