Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ስለ አዲሱ የዓባይ ድልድይ ዘጠኝ ነገሮች

1. ከፊትና ከኋላ ከግራና ከቀኝ በ18 ኬብሎች በአጠቃላይ በ72 ኬብሎች (ገመዶች) የተወጠረ ሆኖ ጠቅላላ ክብደቱ በገመዶቹ አማካኝነት ወደ ቋሚው ምሰሶ የሚተላለፍና ከምሰሶውም ወደ መሰረቱ የሚዘልቅ ነው፣

2. የቋሚው ምሰሶ ከመሰረት በላይ 7 ሜትር ከፍታ እና ታወሩ 27 ሜትር ከፍታ ሲኖረው ከውሃና ከመሬት በታች እስከ 24 ሜትር ጥልቀት ባላቸው በርካታ ፓይሎች የተዋቀረ ነው፣

3. አጠቃላይ የድልድዩ ርዝመት 380 ሜትር ነው፣

4. የጎን ስፋቱ 43 ሜትር ሲሆን በግራና በቀኝ በአንድ ጊዜ 6 ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ ይችላል፣

5. የብስክሌት ተጠቃሚዎች መስመር በሁለቱም አቅጣጫ እንዲሁም 5 ሜትር የእግረኛ መሄጃን ያካተተ ነው፣

6. አንዱን አካባቢ ከሌላው ጋር በማስተሳሰር የምርትና የሸቀጥ ልውውጥን ያለእንግልት በቀላሉ እንዲያከናውኑ ይረዳል፣

7. የወንዙን አቅጣጫ የማስቀየስ ስራ ሳይከናወን በሀገራችን ብዙም ያልተለመደ እና አዲስ ቴክኖሎጂ (ማለትም ተንሸራታች የሆነ ብረት የድልድይ አቃፊ) ግብዓት በመጠቀም መሠራቱ፣

8. በድልድዩ መወጠሪያ ገመዶች ላይ የተለየ መስተጋብር መስጠት የሚችሉ መብራቶች የተገጠሙ መሆኑ እንዲሁም

9. አጠቃላይ የግንባታ ወጪ 1 ቢሊየን 437 ሚሊየን ብር ነው ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መረጃ አመልክቷል።

Exit mobile version