Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ልዑክ ሰመራ ገባ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)የውሀና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር ኢ/ር)፣ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር አይሻ መሀመድ(ኢ/ር)፣ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ለተለያዩ የልማት ስራዎች ጉብኝት አፋር ክልል ሰመራ ከተማ ገብተዋል።

የአፋር ክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በሱልጣን ዓሊሚራህ ሀንፍሬ የአየር ማረፊያ ተገኝተው ለልዑኩ አቀባበል አድርገዋል።

ልዑኩ በአፋር ክልል የተለያዩ አካባቢዎች የበጋ መስኖ ስንዴን ጨምሮ የተለያዩ የግብርና ልማት ስራዎችን እንደሚጎበኝ ተገልጿል።

በታሪኩ ወ/ሰንበት

Exit mobile version