Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የባህል ፌስቲቫልና የቱሪዝም አውደርዕይ  በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው

 

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ)ክልላዊ የባህል ፌስቲቫልና የቱሪዝም አውደርዕይ  የመክፈቻ መርሃ ግብር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል  በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

 

በክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ “የባህልና ቱሪዝም ሀብቶቻችን ለመቻቻል፣ ለሰላማችንና ለሁለንተናዊ ብልፅግናችን” በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀው የባህል ፌስቲቫልና የቱሪዝም አውደ ርዕይን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ  ከፍተዋል፡፡

 

በመክፈቻ መርሃ-ግብሩ ከርዕሰ መስተዳድሩ በተጨማሪ  ሌሎች የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የዞን አመራሮች እና ተጋባዥ እንግዶች መገኘታቸውን ከክልሉ ርእሰ መስተዳደር ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

የባህል ፌስቲቫልና የቱሪዝም አውደርዕዩ  ለተከታታይ ሁለት ቀናት እንደሚካሄድና በመርሃ-ግብሩም በክልሉ የሚገኙ  ብሔር ብሔረሰቦች የህዝብ ለህዝብ ትስስራቸውን ከማጠናከር ባለፈ የባህልና ቱሪዝም ሀብቶቻቸውን እንደሚያስተዋውቁ ተገልጿል፡፡

 

 

Exit mobile version