Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አየርመንገዱ የሀገር ውስጥ መንገደኞች ተርሚናልን አስመረቀ

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአዲስ አበባ በ50 ሚሊየን ዶላር ብር ማስፋፊያ እና እድሳት ያከናወነበትን የሀገር ውስጥ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል አስመርቋል።

በምርቃ መርሐ ግብሩ ላይ የቱሪዝም ሚኒስትሯ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ እና የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር ዴኤታ በርኦ ሀሰንን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የተርሚናሉ ወደ ስራ መግባት በየዓመቱ አየር መንገዱ የሚያስተናግዳቸውን ተጓዦች ቁጥር እንደሚያሳድገው እና ጉዞውን ለማቀላጠፍ እንደሚያስችል ነው የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው የገለፁት።

ተርሚናሉ 4 ከአውሮፕላን ጋር ተገጣሚ የሆኑ በሮች፣ 10 አውቶብስ መሳፈሪያ በሮች፣ 22 ቼክ ኢን ማድረጊያ ስፍራዎችን ጨምሮ በርካታ አገልግሎቶችን መስጠት የሚችል መሆኑን ነው ስራ አስፈፃሚው ያነሱት ።

አየር መንገዱ በየዕለቱ ከ200 በላይ የሀገር ውስጥ በረራዎችን እንደሚያከናውን የገለፁት ዋና ስራ አስፈፃሚው በቅርቡ ወደ ነቀምት እና አክሱም በረራዎች እንደሚጀመሩም ገልፀዋል፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትሯ አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ ÷ቱሪዝም እና በረራ ተያያዥነት እንዳላቸው ገልፀው አየር መንገዱ የተርሚናል ማስፋፊያ ስራዎችን ማከናወኑ የቱሪዝም ዘርፉን እንደሚያግዘው ተናግረዋል።

ተርሚናሉ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እና ኢትዮጵያውያንን ያከበረ መሆኑ ነው የተገለፀው።

የተርሚናሉን ማስፋፊያ እና እድሳት ያከናወነው “ሲሲሲሲ” የተሰኘው የቻይና ኩባንያ ሲሆን÷ የማማከሩን ስራ ደግሞ ዳር ኩባንያ አከናውኖታል ተብሏል።

በፍቅርተ ከበደ

 

Exit mobile version