አዲስ አበባ፣ ግንቦት10፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደርን ጎብኝተዋል።
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ የሳይበር ታለንት ልማት ማዕከልን፣ የአስተዳደሩን የዲጂታል ኤግዚቢሽን፣ ይፋዊ ቁልፍ መሰረተ ልማት ጨምሮ የተቋሙን የተለያዩ የሥራ ክፍሎች አስጎብኝተዋቸዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገሪቱን የሳይበር ደህንነት ለማረጋገጥ በአስተዳደሩ እየተሰሩ ያሉ ዋና ዋና ሥራዎችን መመልከታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።