Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የመዲናዋ የኮሪደር ልማት በአዲስ የሥራ ባህል በተቀናጀ መልኩ እንደቀጠለ ነው – አቶ ጥራቱ በየነ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት በአዲስ የሥራ ባህል በተቀናጀና በተፋጠነ መልኩ የቀጠለ መሆኑን በምክትል ከንቲባ ማእረግ የከተማዋ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ጥራቱ በየነ ገለጹ።

የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት የኢኮኖሚ፣ ኢንቨስትመንትና በተለይም የቱሪዝም እንቅስቃሴን በማሳለጥ ረገድ ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑ ተገልጿል፡፡

በመሆኑም የፕሮጀክቱን ክንውን ክረምቱ ሳይገባ ለማገባደድ ይቻል ዘንድ እየተሰራ መሆኑን የከተማ አስተዳድሩ አስታውቋል።

አቶ ጥራቱ በየነ ፥ በአምስት አቅጣጫዎች እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት በተቀናጀና በተፋጠነ መልኩ መቀጠሉን ገልጸዋል።

የፕሮጀክቱ ክንውን አዲስ የስራ ባህል የተፈጠረበት ትልቅ ስኬት መሆኑን ጠቅሰው ፥ በሁሉም አቅጣጫዎች በተቀናጀና በተቀላጠፈ አግባብ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ይህም የልማት ስራን በጥራትና በፍጥነት ሌት ከቀን ማከናወን እንደሚቻል አዲስ ልምድ የተቀመረበት መሆኑን ጠቅሰዋል።

ከቦሌ መገናኛ ሲኤም ሲ የኮሪደር ልማት ንዑስ ኮሚቴ አስተባባሪ ኤፍሬም ግዛው(ዶ/ር) እና የመገናኛ ሲኤም ሲ ፕሮጀክት አስተባባሪ ከማል ጀማል በበኩላቸው ፥ የኮሪደር ልማቱ የስራ እድል ብቻ ሳይሆን የስራ ባሕልና አስተሳሰብንም የቀየረ ነው ብለዋል።

መንግስት ለዘርፉ ልማት ከፍተኛ ገንዘብ በመበጀትና ልዩ ትኩረት በመስጠት ለሕዝብ ተጠቃሚነት እየሰራ እነደሆነ መግለጻቸውንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Exit mobile version